ራዕይ፣ተልዕኮና እሴቶች
የተቋሙ ተልዕኮ፤ ራዕይና እሴቶች
ተቋሙ በ2017 ዓ.ም በሕዝቦች ተሳትፍና መፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ ድሞክራሲያዊ ሥርዓትና መልካም አስተዲደር የሰፈነባት፣ ማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት፣ ከድህነት ተላቃ መካከለኛ ገቢ ያላት ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ እንደሀገር የተቀመጠውን ራዕይ ከግብ ለማድረስ የራሱን ድርሻ ለመወጣት በተሰጠው ስልጣንና ተግባር መሰረት የራሱን ተልዕኮና ራዕይ እንደሚከተለው አስቀምጧል፡፡
ተልዕኮ
አስፈፃሚ አካላት ሥራቸውን በሕግ መሠረት የሚያከናውኑ መሆኑን መቆጣጠር፣ አስተዲደራዊ በደልን አስመልክቶ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በመመርመር የመፍትሄ ሀሳብ መሻት፣ነባር ሕጎችና አሠራሮች እንድሻሻለ፣ አዳድስ ሕጎች እንድወጡ በማሳሰብ እና አስተዲደራዊ ጥፋቶች የሚሻሻሉበትን ሁኔታ በማጥናት ሀሳብ ማቅረብ፣ ግሌጽነትና ተጠያቂነትን ለማስፈን የሕብረተሰቡንና የአስፈፃሚውን አካል ግንዛቤ በማዳበር፣ የመረጃ ነፃነት ሕግን ማስተግበርና መልካም የመንግሥት አስተዲደርንና የግልጸኝነት ባህልን ማረጋገጥ፡፡
ራዕይ
በ2017 ዓ.ም ግልፅ፣ ቀልጣፋና ተጠያቂ የመንግሥት አስተዲደር እንድሰፌን በማድረግ ውጤታማና ተዓማኒ የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ሆኖ መገኘት ነው፡፡
እሴቶች
- ገለልተኛነትና አለማዳላት /Independency and impartiality/
- እኩልነት፣ ፍትሃዊነትና ርዕታዊነት (Equality, Justice and Fairness)
- ቅልጥፍናና ውጤታማነት (Effectiveness Efficiency)
- ተጠያቂነትና ግልጽነት /Accountability and Transparency/
- ምስጢር ጠባቂነት /Confidentiality/ ፣
- የቡድን ሥራ ለስኬት /Team work/ የሚሉ ናቸው፡፡