By P Web Design Company

ወደህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቌም ድረ-ገፅ እንኳን ደህና መጡ::
ኢትዮጵያ 17ኛውን የአፍሪካ ዕንባ ጠባቂዎች ጥናት ማዕከል የቦርድ ስብሰባ አስተናገደች PDF Print E-mail
ማክሰኞ, 06 February 2018 10:48

ኢትዮጵያ 17ኛውን የአፍሪካ ዕንባ ጠባቂዎች ጥናት ማዕከል የቦርድ ስብሰባ አስተናገደች፡፡ ስብሰባው የተካሔደው ዕለተ ሐሙስ ጥር 17 ቀን 2010 .ም በአዲስ አበባ ነው፡፡

የአፍሪካ ዕንባ ጠባቂዎች ማሕበር ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ ፎዚያ አሚን በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለፁት የአፍሪካ ዕንባ ጠባቂዎች ማሕበር መልካም አስተዳደርን፣ የህግ የበላይነትንና ሰብዓዊ መብቶችን በማስከበር ሂደት በተጓዛቸው ጉዞዎች ሁሉ የአፍሪካ ዕንባ ጠባቂዎች ጥናት ማዕከል አግባብና ወቅቱን የጠበቀ ድጋፍ እየሰጠ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም ማዕከሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመመርመርና በመለየት ብሎም የዕንባ ጠባቂን ሚና በአፍሪካ በማስተዋወቅ ረገድ ጉልህ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል፡፡ ማዕከሉም መልካም አስተዳደር ላይ በሚሰራቸው ጥናትና ምርምሮች እንዲሁም ለአፍሪካ ዕንባ ጠባቂዎች ማሕበር በሚያዘጋጃቸው የኮንፈረንስ ዕቅዶችና የልምድ ልውውጦች ዕውቅና በመስጠት አመስግነዋል፡፡

በተጨማሪም የአፍሪካ ዕንባ ጠባቂዎች ማሕበር የአፍሪካ ሕብረት በ2020 .ም የተኩስ ድምፅ በአህጉሯ እንዳይሰማ ያነገበውን ዓላማ በመደገፍ ከማዕከሉ ጋር በጥምረት ለመስራት ያላቸውን ዝግጁነት አሳውቀዋል፡፡

በስብሰባው ላይ የአፍሪካ ዕንባ ጠባቂዎች ጥናት ማዕከል የቦርድ ሊቀ-መንበር ክብርት ቡሲሲዌ ሙኳባኔ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክትም የአፍሪካ ዕንባ ጠባቂዎች ማሕበርና የአፍሪካ ዕንባ ጠባቂዎች ጥናት ማዕከል ለአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 መሳካት የበኩላቸውን ጥረት እንደሚያደርጉ አመላክተዋል፡፡

የመልካም አስተዳደር እንዲሁም ሰላምና መረጋጋትን በአፍሪካ የማስፈን ሂደት ለነገ የማይባል በጣም አሳሳቢ ጉዳይ እንደሆነ ገልፀው ማሕበሩበእንደዚህ አይነት ጉዳዮች ላይ ጣልቃ በመግባት ግጭቶችን የመፍታት ስራ ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

መጨረሻ የተሻሻለው በ ማክሰኞ, 06 February 2018 10:56
 
ግልጸኝነት፣ የመረጃ ተደራሽነትና ፋይዳው PDF Print E-mail
ማክሰኞ, 30 January 2018 09:07

ብዙ ጊዜ የተለያዩ አካላት የመረጃ ተደራሽነት እና ግልጸኝነትን ተመሳሳይ ትርጉም በመስጠት ሲጠቀሙበት ይስተዋላል፡፡ ይሁን እንጅ በሁለቱ መካካል የትርጉም ልዩነቶች እንዳሉ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

የግልጸኝነት መርህ በዴሞክራሴያዊ መንግስትና ህብረተሰብ ውስጥ ከፍተኛ ዋጋ ያለው መሰረታዊ ግብዓት ነው፡፡ በተለይም በዴሞክራሴያዊ የመንግስት ስርዓት አሰራር ውስጥ ግልጸኝነት የሰፈነበት የመንግስት አሰራር ውስጥ መንግስት የሚሰራቸውን ስራዎችና የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በግልጸኝነጽ መንፈስ ማከናወን እንዳለበት ይታመናል፡፡ በኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 12 ላይም በግልጽ ሰፍሮ ይገኛል፡፡ በዚህ መሰረትም ግልጸኝነት የሰፈነበት የመንግስት አሰራር ስንል አብዛኛውን ጊዜ መንግስት የሚሰራቸውን ስራዎች የሚያሳዩ መረጃዎችን፣ የሚጠቀምባቸውን ፖሊሲዎችና ስትራቴጅዎች ጨምሮ ሌሎች መረጃዎች ለህዝቡ ተደራሽ ማድረግ ሲችል ነው፡፡ ይህ መሆን ሲችል ነው የመንግስት አሰራሩ ግልጸኝነት የሰፈነበት ነው ሊባል የሚችለው፡፡ ይሁን እንጅ መንግስት እያንንዱን እንቅስቃሴ ከህብረተሰቡ የሚሰውር ከሆነ ግልጸኝነት አለ ብሎ ለመናገር የሚያስቸግር ይሆናል፡፡

በመሆኑም ግልጸኝነት መረጃዎችን ለህዝብ ይፋ በማድረግ የሚገኝ ውጤት እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ስለዚህ ግልጸኝነት እንዲሰፍን መረጃዎች ተደራሽነት መኖር ወሳኝ ሚና አላቸው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡ ለዚህም ነው ጸሀፊዎች ‹‹ A transparent public body is one that is characterized by visibility or accessibility of information by people›› በማለት የሚገልጹት፡፡ መረጃዎችን ግልጽ ሊገኙ በሚችሉና ተደራሽ እንዲሆኑ ማድረግ ግልጸኝነት ለሰፈነበት አሰራር መሰረታዊ እንደሆኑ የተለያዩ ሙህራኖች ይናገራሉ፡፡ እንመለከታለን፡፡ ስለሆነም የመንግስት ተቋማት መረጃዎችን ሲጠየቁ መስጠት ብቻ ሳይሆን ሳይጠየቁም መረጃዎችን አሳትሞ ለተጠቃሚው የማዳረስ ግዴታ እንዳለባቸው በመረጃ አዋጁ ተደንግ፡፡ ለለአብነትም በ ድረ ገጾችና በሶሻል ሚዲያዎች፣ በተለያዩ መጽሄቶችና የህትመት ውጤቶች አማካኝነት አሳትሞ ማሰራጨት እንዳለባቸው ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ የመረጃ ግልጸኝነት መኖርና መንግስት አሰራሩን ለህዝብ ግልጽ ሲያደርግ የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ ሲሆን ለአብነት ለመጥቀስ ያህል፡-ለተጠያቂነት (Accountability)

ተጠያቂነትን ያለ መረጃ ለመፍጠር መሞከር ትርጉም እንደሌለው አያጠያይቅም፡፡ መጠየቅ ያለባቸውን አካላት ተጠያቂ ማድረግ የምንችለው የተደራጀ መረጃ ሲኖር ብቻ መሆኑ እሙን ነው፡፡ ህዝቡም የተለያዩ አካላትን በህግ በመጠየቅ እንዲጠየቁ ማድረግ የሚቻለው መረጃዎች ግልጽ መሆን ሲችሉ ነው፡፡

ለተሳትፎ (participation):- በዴሞክራሲ ግንባታ ሂደት ውስጥ ህብረተሰቡ በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ ተጽእኖ በሚያሳድሩ ጉዳዮች ላይ በሚገባ ለመሳተፍ እንዲችል ሰፊ የሆነ መረጃ የሚሰበስብበት ሁኔታ ሊኖር ይገባል፡፡ ይህ ደግሞ በዴምክራሲና መልካም አስተዳደር ላይም ሆነ በሌሎች ጉዳዮች ላይ ለመሳተፍና ለመወሰን የግዴታ መረጃ መኖር ያስፈልጋል፡፡ ዜጎች በአገራዊ ፣በማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ በሰፊው መሳተፍ እንዲችሉ የመረጃ ተደራሽነት አስፈላጊ ነው፡፡

አቅምን ለመገንባት (Transparency for efficiency)

ተቋማት መረጃዎችን በሚጠየቁ ጊዜ የመስጠት አቅማቸው ከፍ እያለ ሲሄድ መረጃዎችን በአግባቡ አደራጅቶ የመያዝ ባህላቸው እየጎለበተ ይሄዳል፡፡ ይህ ማለት ደግሞ መረጃን በፍጥነት ከመስጠት በተጨማሪ ትክክለኛና ሚዛናዊ ውሳኔ ለማስተላለፍ ያለው ፋይዳ የጎላ ነው፡፡ በተጨማሪም በተቋማትና በማህበረሰቡ መካከል የተሻለና የተሳለጠ ግንኙነት እንዲኖር ያስችላል፡፡ በመሆኑም ግልጸኝነትም ሆነ የመረጃ ተደራሽነት በአንድ አገር ውስጥ የዴሞክራሲ ስርዓትና መልካም የመንግስት አስተዳደር እንዲሰፍን ከማድረግ አንጻር ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ ሁሉም አስፈጻሚ፣ባለድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ ለአፈጻጸማቸው የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንደወጡ ተቋሙ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

መጨረሻ የተሻሻለው በ ማክሰኞ, 30 January 2018 09:30
 
በፀደቀው የመረጃ ነጸነት ደንብ ላይ ስልጠና ተሰጠ PDF Print E-mail
ሐሙስ, 05 October 2017 08:06

የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በአገራችን ግልፅነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት መልካም የመንግስት አስተዳደር መገንባት ለዜጎች ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ተጠቃሚነት ወሳኝ እንደሆነ ያምናል፡፡ ከዚህ አላማ በመነሳት መልካም የመንግስት አስተዳደር የሰፈነበት ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት ብሎም ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የተለያዩ አሰራሮችን በጥናትና በቁጥጥር በመፈተሸ ለተግባራዊነቱ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ተቋሙ እያስፈፀመ የሚገኘው የመገናኛ ብዙሃንና የመረጃ ነፃነት አዋጅ ቁጥር 59/2ዐዐዐ በክፍል 3 ስር የተዘረዘሩትን እያስተገበረ ይገኛል፡፡ በዚህም ረገድ ልዩ ልዩ የህግ ማዕቀፎችን፣ ቼክሊስቶችንና መመሪያዎችን በማዘጋጀት በየወቅቱ ስራ ላይ እያዋለ ይገኛል፡፡

ተቋሙ የመረጃ ነፃነት አዋጁ ለመልካም አስተዳደርና ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማበርከት የሚችለውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት ብሎም ሕብረተሰቡ በመንግስት የስራ እንቅስቃሴዎች ላይ መረጃ ጠያቂና በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ንቁ ተሣታፊ እንዲሆን በተለያዩ አግባቦች ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ከዚህም ጎን ለጎን ዜጎች በአዋጁ ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተጨማሪ የአዋጁ ማሟያና አጋዥ የሆኑ ማዕቀፎችንና ደንቦችን እያዘጋጀ እና እየሰራበት ይገኛል፡፡

ለአብነት ከእነዚህ ደንቦች መካከል ሚያዝያ 17/2009 .ም በሚኒስትሮች ም/ቤት የፀደቀው ለሕዝብ ጥቅም መረጃ ይፋ የማድረግ ደንብ አንዱ ነው፡፡ በደንቡ ላይ አቶ ይርሳው ዘውዴ ለፌዴራል የኮሙኒኬሽን ከፍተኛ አመራሮች፣ ለክልል የሕዝብ ግንኙነት የቢሮ ሃላፊዎችና ለፌዴራል ሚኒስትር መ/ቤቶች የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊዎች መስከረም 8 እና 9 ቀን 2010 .ም በአዳማ ከተማ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡

በስልጠናው እንደተመለከተው የመረጃ ነፃነት አዋጁ በአንቀፅ 39/2 እና 3 የሕዝብ ጥቅም የሚያረጋግጡ መረጃዎችን ይፋ የሚያደርጉ ሰዎች የፍትሐ-ብሔርም ሆነ የወንጀል ተጠያቂነት እንደማይኖርባቸው፣ የሕዝብ ጤንነትንና ደህንነትን፣ የአካባቢያዊ ደህንነትንና ጎጂ የሆነ ከባድ አደጋን በሚመለከት መረጃን ይፋ ማድረግ እንደሚቻል የሚደነግግ በመሆኑ ደንቡ የዚህን ድንጋጌ የተሟላ ተፈፃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ተገልል፡፡

በመሆኑም የመንግስት አካላት በተለይም የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊዎች መረጃዎችን ሃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ ለመረጃ ፈላጊዎች መስጠት የሚችሉበትን ስርዓት በመዘርጋት ለግልፅነትና ለተጠያቂነት አሠራር መጎልበት እንዲሁም ለደንቡ ተፈፃሚነት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ በስልጠናው ላይ ተመልክቷል፡፡

የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋምም መልካም የመንግስት አስተዳደርን ማስፈን ትልቅ አገራዊ አጀንዳ መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት መረጃን ለህዝብ ጥቅም ይፋ የማድረግ አሠራርን በህግ ማዕቀፍ አስደግፎ ተግባራዊ ለማድረግ ከህጉ ረቂቅ ጀምሮ በሚኒስተሮች ምክር ቤት በመገናኛ ብዙሃንና የመረጃ ነፃነት አዋጅ ቁጥር 59/2ዐዐዐ አንቀፅ 37/3 መሠረት እስኪፀድቅ እና በነጋሪት ጋዜጣ እስኪታወጅ ድረስ ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የራሱን ሃላፊነት ሲወጣ ቆይቷል፡፡ በቀጣይነትም ተቋሙ ዜጎች በመልካም አስተዳዳር ዕጦት እንዳይጉላሉና መረጃን በነፃነት መስጠትም ሆነ መቀበል እንዲችሉ አለኝታ ሆኖ መብቶቻቸውን እንዲከበር ከወትሮው በበለጠ ሁኔታ ይሰራል፡፡

በመጨረሻም በመድረኩ ላይ የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ም/ዋና ዕንባ ጠባቂ የሆኑት ክብርት ወ/ሮ ሰራዊት ስለሺ ለደንቡ ተፈጻሚነት ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ በተለይም የፌዴራልና የክልል የሕዝብ ግንኙነት አካላት የተጣለባቸውን ሃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ስለ ደንቡ ዝርዝር ማብራሪያ እና ይዘት ለመረዳት ሚያዝያ 17/2009 የፀደቀውን ደንብ ከኢ.... ነጋሪት ጋዜጣ ላይ ይመልከቱ፡፡

 
የአፍሪካ ዕንባ ጠባቂዎች ማህበር የአፍሪካ የሰላም ሽልማት አገኘ PDF Print E-mail
ሐሙስ, 13 July 2017 09:45

ኢትዮጵያ በፕሬዝዳንትነት እየመራች ባለችው የአፍሪካ ዕንባ ጠባቂዎች ማህበር፣ በአፍሪካ በመልካም አስተደደር ንባታ፣ በሰላም አብሮ የመኖር እሴቶችን በማጠናከር እና የህግ የበላይነትን እንዲሰፍን በማድረግ እያበረከተ ባለው ውጤታማ ስራ ዩናይትድ ሪሊጂንስ ኢኒሼቲቭ የሚባል አለማቀፍ ተቋም የአፍሪካ የሰላም ሽልማት አበርክቶለታል፡፡

 

በቡሩንዲ ዋና ከተማ ቡጅምቡራ ከ 29-30/2009 .. ሲካሄድ በቆየው አለማቀፍ የሰላም ኮንፈረንስ ላይ ይህ የዕውቅና ሽልማት ለማህበሩ በተሰጠበት ወቅት የህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዋና ዕንባ ጠባቂ እና የማህበሩ ፕሬዝዳንት /ሮ ፎዚያ አሚን እንደተናገሩት ‘የተሰጠው ሽልማት ማህበሩ በአፍሪካ የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ፣ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ እና መልካም የመንግስት አስተዳደር እንዲሰፍን ተግቶ እንዲሰራ የበለጠ ያበረታታዋል‘ ብለዋል፡፡

Hon. Foziya Amin

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የዩናይትድ ሪሊጂንስ ኢንሼቲቭ አፍሪካ ዳይሬክተር የሆኑት አምባሳደር ሙሴ ሀይሉ ሲገልጹ ‘ተቋማችን ይህን ሽልማት ለማህበሩ ሲያበረክት ማህበሩ በሰላም አብሮ የመኖር ዕሴቶች እንዲጠናከሩ፣ መልካም አስተዳደር ስርዓት እንዲገነባ፣ ሰብአዊና ዲሞክራሲ መብቶች እንዲከበሩ እያደረገ ስላለው ጥረትና የሰራቸውን ውጤታማ ስራዎችን በመገምገም ነው‘ ብለዋል፡፡

 

በቀጣይም ተቋማቸው ከአፍሪካ ዕንባ ጠባቂዎች ማህበር ጋር አብሮ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸውንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

መጨረሻ የተሻሻለው በ አርብ, 14 July 2017 07:28
 
African Ombudsman& Mediators Association observes the 26th African Union Summit PDF Print E-mail
ሐሙስ, 04 February 2016 13:28

Addis Ababa ,January 2016-Ethiopian Institution of the Ombudsman, Chief Ombudsman Foziya Amin - President of African Ombudsman & Mediators Association (AOMA) attended on the 26th African Union Summit which was held from January 30-31/2016 under  the theme "2016: African Year of Human Rights with a particular focus on the Rights of Women” at the headquarters of  the Union Addis Ababa ,Ethiopia with a capacity of observer status representing  AOMA as per the agreement signed between AU-AOMA in October 2011

AU Summit

The Chairperson of the African Union Commission, Dr. Nkosazana Dlamini Zuma in  her welcoming  Remarks  to the 26th Ordinary Session of the Assembly of Heads of State and Government Addis Ababa said   that Africa  must continue to place its  people and their basic human rights, at the centre of Agenda 2063.

 

"This includes our people’s rights to education, to food and nutrition, to health care, to safe water, sanitation and energy, to join in peace, to be safe from violence and extremism, to reach their full potential, in addition to the right to association, to free speech, to freedom of the media and to be protected from discrimination on any grounds. We are making progress, but our pace is very slow. We must use 2016 as a platform to advance these human rights of all
the inhabitants of our continent, in their full diversity, as we work together to create the Africa we want,"  said  the Chairperson of the African Union Commission.

H.E. Idriss Deby Itno, Chairperson of the African Union brought the 26th Ordinary session of the African Union to an end with his remarks appreciating the environment and atmosphere of the Summit which was peaceful. He also thanked the Assembly for their recommendations in respect of the fight against terrorism in Africa. President Deby appealed to all Member States to take seriously, issues which undermine the development of Africa. Dialogue is the key, AU
Chairperson said. In addition, he appealed to the African Union to strengthen its efforts to find ways of bringing peace to Burundi and South Sudan. “We cannot tolerant violence which kills thousands of Africans and leaves them displaced, let us all be vigilant and listen
to the cries of our people.”

The new AU Chairperson would have among other important duties to ensure the implementation by AU Member States of the theme 2016: African Year of Human Rights with a particular focus on the Rights of Women and the Ten Year Implementation Plan of Agenda 2063. He would further mobilize the continent to implement the AU Agenda 2063 with
the view to place Africa as a key player in the world arena.

 

The  Summit has brought   together, including AOMA representative  ,  policy making Organs of the Union, representatives from the Regional Economic Communities (RECs), Civil Society Organizations (CSOs), the Private Sector, the Diaspora, partner organizations, continental and international media and dignitaries as well as invited guests world-wide.

መጨረሻ የተሻሻለው በ ሐሙስ, 04 February 2016 13:47
 
<< Start < Prev 1 2 3 4 Next > End >>

Page 1 of 4